እነዚህ የቦርድ መሸኛ ወረቀታቸው ወደ ሚኖሩበት ወረዳ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚላክላቸው የተነገሩት ከሰራዊቱ
ተሰናብተው የሄዱ ወተሃደሮች ከተባሉት ቀን በኋላ በወረዳቸው ሄደው በተጠየቁበት ሰአት ስለምትሉት ነገር የምናውቀው ነገር የለም
ስለተባሉ ወደ ክልል ቢሄዱም የተለየ መልስ ስላላገኙ ወደ ነበሩበት ክፍል ተመልሰው ለምን እንዳልተላከላቸው በጠየቁበት ግዜም ሂዱና
በቦታችሁ ሆናችሁ ጠብቁ በማለት አስፈራርተው እንዳባረሯቸው ምንጮቻችን ከቦታው አስታውቀዋል።
መረጃው በማስከተል እነዚህ ከሰራዊቱ
ያለምንም መሸኛ በቃል ብቻ ተነግረው የተሰናበትቱን ወገኖች የቦርድ ወረቀታቸውን ለማግኘት ከወረዳ ጀምረው እስከ ክልል እንዲሁም
እስከነበሩበት ክፍል እየተመላለሱ ለከፍተኛ ወጪ እንደተጋለጡና ለከፋ
ማህበራዊ ኑሮ መውደቃቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።