Friday, July 25, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ የሚገኙ የወያኔ ኢህአደግ ሰራዊት በመካከላቸው የብሄር ልዩነት ግጭት እንደተፈጠረ ከሰራዊቱ ውስጥ ሸልኮ የደረሰን መረጃ ገለፀ።



    በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ የሚገኙ የወያኔ ሰራዊት አባላት በብሄርና በዘር እየተለያዩ በካባድ ቅራኔ ውስጥ መግባታቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ ምክንያት  ብዙ የሰራዊት አባላት ክፍላቸው ትተው እግራቸው ወደ አመራቸው እየጠፉ መሆናቸውን ተገለፀ።
    በስራዊቱ መጥፋት ምክንያት የተደናገጡ የአከባቢው አስተዳደሪዎች አቶ ልኡል ገብሩና የወረዳው ሃላፊ ሃለቃ ገረንቸኣል በአከባቢው ለሚገኝ ህዝብ ሰብስበው ሌላ አማራጭ ስለሌለ አከባቢያችሁን ራሳችሁ ጠብቁ ብለው ትእዛዝ ማውረዳቸውና የአከባቢው ህዝብ በበኩሉም መከላከያ ሰራዊቱ ሃገርን ጠብቆ ያልቻለው እኛ የማንችለውና ከአቅማችን በላይ ነው ሲሉ የተቃውሞ ምላሽ እንደመለሱሏቸው ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።