Friday, July 25, 2014

በትግራይ ማእከላዊ ዞን የአሕፈሮም ወረዳ ነዋሪዎች ከደምህት ግንኙነት አላችሁ በሚል ምክንያት ንፁሃን ወገኖችን በመቐለ ከተማ ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ካከባቢው የተገኘው መረጃ አመለከተ።



ሚያዝያ 21/2002 ዓ/ም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በአሕፈሮም ወረዳ ቀበሌ፤ የውንጥሕና ለይቶ አከባቢ በወያኔ ኢህአደግ ሰራዊት በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ከባድ ኪሳራ እንደደረሰበት የሚታወቅ ሆኖ የዚህ ቅጣት ለመመለስ ብሎ የአከባቢውን ህዝብ በውጊያው ወቅት ለትህዴን መንገድ መርታቹሁ በሰራዊታችን ላይ ከባድ ኪሳራ እንዲያደርስ ምክንያት ሆናችኋል በሚል ሰበብ በስርአቱ ተላላኪዎች ንፁሃን ወገኖች ባልዋሉበት ወንጀል መቐለ ከተማ ውስጥ እስከ አሁን ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
   መቐለ ከተማ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ ካሉ ንፁሃን ዜጎቻችን ፀጋይ ሞጎስ፤ በሃበሎም መለስና ዮናስ የተባሉ ሲሆኑ በአጠቃላይ የስርአቱ ካድሬዎች ለአከባቢው ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ከትህዴን) ሰራዊት ጋር እየተገናኛችሁ ምግብና ውሃ ታቀርባላችሁ እየተባሉ በስርአቱ ካድሬዎች እየተንገላቱ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።