Wednesday, September 10, 2014

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋና ፊቕ ከተማዎች ውስጥ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ለሁለት ሳምንት ያኽል የመብራትና የስልክ አገልግሎት እንደተቋረጠ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት የመብራት፤ የውሃና የስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ቢቆይም ያሁኑ ግን በባሰ መልኩ ከሁለት ሳምንታት በላይ ካገልግሎት ውጭ ሆኖ መቋረጡና እስካሁን ድረስም ምንም አይነት መፍትሄ ባለማግኘቱ ምክንያት የጅግጅጋና የፊቕ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ብሶቱን እያሰማ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር /ኦ.ብ.ነ.ግ/ ጋር ይቀራረባሉ ብለው ለፈረጅዋቸውና ለፈሯቸው የከተማው ነዋሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙ ዘግቶዋቸው እንደሚገኙና የፊቕ ነዋሪዎችም ከተቃዋሚዎቹ ጋር ግንኝነት አላችሁ እየተባሉ በስርአቱ ሃይሎች እየታሰሩ እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል።