Wednesday, September 10, 2014

የገዥው ፓርቲ መሪዎች የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም ሲሉ በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት የመፍጠር እኩይ ተግባራቸውን በከፋ መልኩ እየቀጠሉበት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።



የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፀረ ህዝብ ባለ-ስልጣኖች  በሃገራችን  ብሄር ብሄረሰቦችን የማጣላትና የማጋጨት የተለመደ ተግባራቸውን በማጠናከር እየቀጠሉበት እንደሚገኙና ይህንን ለመተግበር ደግሞ ንፁሃን ዜጎችን በታጠቁ ሃይሎች እየገደሉ በህዝቦች መካከል መተማመን እንዳይኖር ለማድረግ አበርትተው እየሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከተለያዩ የትግራይና የአማራ አካባቢዎች አስረዱ።
   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። ቀደም ሲል ገዥው መንግስት በአማራና በትግራይ ክልል ተወላጆች መካከል የጀመረው የማጣላት ተግባር እንዲባባስ የተለያዩ  የተንኮል ሴራዎችን በመሸረብ ላይ ሲሆን በቅርቡ በመተማ ወረዳ አራት ሰዎች በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ታጣቂዎች ተገድለው እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
   በተመሳሳይ ነቃ በተባለ ወንዝ ዳር ነሀሴ 24 /2006 ዓ/ም ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ንፁህ ዜጋ ተግድሎ እንደተገኘ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።