Thursday, September 18, 2014

በአገር ደረጃ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲሰጥ የሰነበተውን ሰሚናር ግቡ እንዳልመታና በተማሪዎቹ የቀረቡት ጥያቄዎችም ቢሆን ተገቢ መልስ እንዳልተሰጠባቸው ተገለፀ።



    ይህ በመላው ሃገሪቱ ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች በስርአቱ ካድሬዎች ሲሰጥ የሰነበተው ሰሚናር አላማው ተማሪዎቹን በገዥው መንግስት እጅ እንዲገቡ ለማድረግና 2007 ዓ/ም በሚካሄደው አስመሳይ ምርጫ ላይ ደጋፊዎች ሆነው እንዲቀርቡ ያለመ መሆኑን ቢታወቅም ለቅስቀሳ ተብሎ የቀረበውን አጀንዳ በተማሪዎቹ ተቃውሞ ስለገጠመው እንደታሰበው ሳይሆን መቅረቱ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
   ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲሰጥ የሰነበተውን ሰሚናር ያለፉትን ስርአቶች ታሪክ የሚወቅስ ቢሆንም ተማርዎች ግን ካለፉት ስርአቶች የናንተው ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድና ወጀሎች ይብሳል በማለት በስርአቱ ላይ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች ምንጮቻችን ገለፁ።
   መረጃው በማስከተል በአዲ ግራት፤ መቐለና አክሱም ከተሞች ሰሚናር ሲወስዱ የሰነበቱትን ተማሪዎች የህወሃት ኢህአዴግ ታሪክ ከሚገባው በላይ በማርገብገብ የተክሄደውን ቅስቀሳ እንዳልተቀበሉትና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እየተገኙና እየተነጋገሩበት መሆናቸውን ለማወቅ ተችለዋል።