Friday, September 12, 2014

የእንደርታ ወረዳ እግሪ ሓሬባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወገኖቻችን በብሉሹ አስተዳደር ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን ችግር በሰለማዊ መንገድ ስለጠየቁ ብቻ እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።



   በመረጃው መሰረት እነዚህ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን እንደርታ ወረዳ እግሪ ሓሬባ ቀበሌ የሚገኙ ወገኖቻችን በገዢው ስርአት ብሉሹ አስተዳደር ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው ችግር እንዲፈታላቸው በማለት በሰለማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን በማቅረባቸው ብቻ በስርአቱ እየታሰሩ  እንደቆዩ የጠቀሰው መረጃው በአሁኑ ስአትም ገዢው ድርጅት ይህንን ተግባሩ እየቀጠለበት መሆኑን ተገለፀ።
     በቀበሌዋ ነዋሪ የሆኑት ቄስ ገብሩና አቶ ገብረሂወት የተባለው የጀኦግራፊ መምህር ነሃሴ 25/ 2006 ዓ/ም በስርአቱ ተላላኪዎች የታሰሩ ሲሆን ኹሓ ከተማ በሚገኘው የወልደ ደንጉስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የእንግሊዝኛ መምህር ገብሩም የመምህር ገብርሂወት ወንድም በመሆኑ ብቻ በካድሬዎችና በፀጥታ አካላት ማስፈራራትና ዛቻ ስለደረስበት ስራውን ትቶ ወደ አዲስ አበባ እንደሄደ ለማወቕ ተችሏል።
   መምህር ገብሩ የእግሪ ሓሬባ ነዋሪ ሆኖው በወረዳው አስተዳዳሪዎችና በፀጥታ አካላት አነሳሾች ተብለው ከተፈረጁት ሰዎች አንዱ እንደሆኑ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።