በመረጃው መሰረት የህወሓት
ኢህአደግ ባለ-ስልጣናት ከነሃሴ 26 2006 ዓ/ም ጀምረው ስልጣን ከድርጅቱ እጅ እንዳይወጣ በማያባራ ስብሰባ ተጠምደው እንዳሉ
በመግለፅ ስብሰባውን እየመሩት ያሉትም በወዲ-ዓድዋ ቅጥያ ስም የሚታወቀው የክፍለ ከተማው የሚልሻ ሃላፊው አቶ ልዑልና የክፍለ ከተማው
አስተዳደር አቶ አማኒኤል ተስፋዮሃንስ እንደሆኑ መረጃው ጨምሮ አመልክቷል።
በነዚህ የበላይ አመራሮች የተመራው ስብሰባ ዋና አላማው የስልጣን ስግብግብነት
ሲሆን የስብሰባው አጀንዳም ያለፉትን ስርአቶች በመኮነንና የገዢውን ድርጅት የትግል ታሪክና ልማታዊ መንግስት የሚል ያረጀ የውሸት
ትንተና እንደሆነ የገለፀው መረጃው ድርጅታችን ልማታዊና ዴሞክራስያዊ ስለሆነ የቕብብል ዱላዋን ከእጃችን እንዳትወጣ እንያዛት በማለት
ለተበላሸው አስተዳደራቸው በህዝባዊ አመፅ እንዳያጡት በመስጋት እንዲጠነቀቁ የሚል እንዳሆነ ለማወቕ ተችሏል።