Friday, October 31, 2014

በላዕላይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ የወያኔ ኢህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ሰርተው ዕለታዊ ኑሮአቸውን የሚመሩ ንፁሃን ዜጎችን ከትህዴን ጋር ትተባበራላችሁ በማለት አስረው እያሰቃዩአቸው እንደሆኑ ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድተዋል፣





በመረጃው መሰረት ጥቅምት 8 2007 ዓ/ም በላዕላይ አድያቦ ወረዳ ምድረ ፈላሲ ቀበሌ ከተለያዩ አካባቢዎች ሄደው በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚለቅሙ ዜጎችን ለትህዴን አባላት መንገድ መርታችኋል ስንቅ አቀብላችኋልና ሌሎችንም ሰንካላ ምክንያቶች በመደርደር 15 ሰዎችን በአዲነብሪኢድ ከተማ አስረው እያሰቃዩዋቸው መሆኑ ታውቋል፣
   በአዲነብሪኢድ ከተማ ታስረው ከሚሰቃዩ ወገኖች የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ተክላይ ገብረመድህንና ሰሎሙን የተባለ ለጊዜው የአባቱ ስም ያልታወቀ ፅገ ወልደዮሃንስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ሲሆኑ እነዚህ ወገኖች የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖር በመታሰራቸው ህግና ስርዓት የሌለው መንግስት ሲሉ ምሬታቸውን እየገለፁ መሆኑን መረጃው አስረድቷል፣