Friday, October 31, 2014

በአብራ ጅራና በአብደ-ራፍዕ መካከል ሰዎች ጭና ስትጓዝ የነበረች መኪና። በኢህአዴግ የፖሊስ አባላት እንደተዘረፈች ምንጮች ከአባቢው አስታወቁ፣





በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በአብራ-ጅራና በአብደ-ራፍዕ መካከል ከ18 በላይ የቀን ሰራተኞች ጭና ስትጓዝ የነበረችውን ሚኒባስ መኪና። የፀጥታ አስከባሪዎች መስለው በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የቆዩት 4 ሚሊሻና ፖሊስ ጨለማን ተገን በማድረግ ከሌሊቱ 3።00 ሰአት መኪናዋ ላይ ተሳፍረው የነበሩትን ሰዎች ፈትሸው ገንዘባቸውን እንደወሰዱባቸው ታውቋል፣
    በታጣቂዎቹ ገንዘባቸውን ከተነጠቁት የተወሰኑትን ለመጥቀስ። ገብረኪዳን ካህሳይ 1,800 ብር፤ ገረንችአል ትኩእ 1,750 ብር፤ ዓወት ትርፈ 2000 ብር፤ ዛይድ የማነ 1,400 ብር እንደሆኑ ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣
     እንዲህ አይነቱ ግለኝነት የተጠናወተው በፖሊስ አባላት የሚፈፀመው ዝርፊያ። በአካባቢው ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመምጣቱ የተነሳ። ነዋሪው ህዝብ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ የሚሰራበት ዋስትና ማጣቱንና ችግር ላይ መውደቁን አስመልክተን ባለፈው የዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል፣
     በተመሳሳይ በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን። በታሕታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ ፖሊሶች። ምንም ወንጀል ላልፈፀሙ ንፁሃን ወገኖቻችን እየገደሉ መሆናቸውን ምንጮቹ በላኩት መረጃ ለመረዳት ተችሏል፣
    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። እነኝህ በታህታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ ፖሊሶች። ዓዲ ሃገራይ ልዩ ሰሙ ዓዲ ተልዖም ወደ ተባለው አካባቢ ሄደው ወርቅ ለቀማ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች። ለምን ባልተፈቀደ ቦታ ሂዳችሁ ወርቅ ለቀማችሁ በማለት እየገደሏቸው እንደሆነ ተገልጿል፣
     በፖሊሶቹና ወርቅ ለቀማ ስራ ላይ በተሰማሩ ወገኖች ጋር በተነሳው ግርግር ምክንያት። ጥቅምት 2/2007 ዓ/ም ነጋሲ ወልደማርያም የተባለ ግለሰብ በፖሊሶቹ እንደተገደለ የገለፀው መረጃው። የዚሁ ወንጀል ፈፃሚና ተጠያቂም ምክትል ኢንስፔክተር ለገሰ መሆኑንና። የሟቹ ቤተሰብም ወደ ፍርድ ቤት ክስ ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣