Friday, October 31, 2014

የገዥው ህወሃት ኢህ.አዴግ ቡድን የፖሊስ አዛዦች የግል ፍላጎታቸውን ለማያሟሉ ከስልጣናቸው በታች ለሚገኙ ሴቶች ስልጣናቸውን ተጠቅመው እያንገላቷቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣





በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኝ  የፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳንኤል።  በስሩ ተመድበው የሚሰሩ ሴት የፖሊስ አባላቶችን ጊዜያዊ የግብረ ስጋ ግንኚነት ሊጠቀም ፈልጎ ስላልተቀበሉት ብቻ ሃላፊነቱን ተጠቅሞ ከተመደቡበት ሙያ አስወጥቶ ዘበኛ ሁነው እንዲሰሩ ማድረጉን ጥቅምት 15 2007 ዓ/ም በዞን ደረጃ በተደረገ ስብሰባ ላይ እንደተጋለጠ ታውቋል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ የፖሊስ አዛዥ  በተለይ ለአንዲት ፖሊስ ግዜያዊ ስሜቱን ለማርካት ሲል ደጋግሞ ጠይቋት ስላልተቀበለችው በሃይል አስገድዶ ሊደፍራት ሞክሮ ሳይሳካለት በመቅረቱ ለአመታት ሰልጥና ስትሰራበት ከኖረችው መስሪያ ቤት አስወጥቶ የዘበኛ ስራ እንድትሰራ ማድረጉን ያወቁ አንዳንድ የፖሊስ አባላቶች በስብሰባው እንዲጋለጥ ማድረጋቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ ምክንያትም በመድረክ መሪው ኮማንደር ገብረኪዳን ኪዳኑ ወዲሽራሮና ምክትል ኮማንደር ዳንኤል መካከል እመን አላምንም ከፍተኛ አለመግባባት  እንድተፈጠረና በግለሰቡ ላይ የተወሰደ ምንም አይነት እርማጃ አለመኖሩን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣