Friday, October 31, 2014

በሃገራችን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ ያሉት ወጎኖቻችን ቁጥራቸው በየ ግዜው እየተበራከተ በመሄድ ላይ እንደሆነ ተገለፀ፣





በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። ጥቅምት 1 / 2007 ዓ/ም በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ “ ገነት ሃውስ “ ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ ጌትነት የማነ የተባለ ዜጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል፣
    መረጃው ጨምሮ እንዳመለከተው። ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች በቁጥጥር ስር ሳይውሉ ሰለተሰወሩ። የከተማው ፖሊሶች ደግሞ እየሰሩ ናቸው እንዲባሉ ብቻ በሆቴሉ አከባቢ ያገኙዋቸውን 5 ሰዎች የወንጀሉ ፈፃሚዎች እናንተ ናችሁ በማለት በጥርጣሬ አስረዋቸው እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ። የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ግን የስርአቱ ካድሬዎች ራሳቸው አቀናብረው የፈፀሙት ወንጀል ነው። በማለት ጥርጣሬአቸውን በመግለጽ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፣
   በተመሳሳይም። በአድዋ ከተማ ጥቅምት 6 / 2007 ዓ/ም ተስፋይ ፍስሃ የተባለ ዜጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሌሊት ከቤቱ አውጥተው እንደገደሉት የገለፀው መረጃው። የወንጀሉ ፈፃሚዎች ማጣራት ተደርጎ በህግ ቁጥጥር ስር ሊውሉ ባለመቻላቸው ምክንያት። የሟች ቤተሰቦች በአስተዳደሩ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በመግለፅ ላይ እንዳሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣