Wednesday, November 26, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ከፖለቲካ አባልነት ነፃ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የኢህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች የሚከተሉት ቅስቀሳ አውዳሚ መሆኑን ገለፁ።



    በደረሰን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ነፃ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ህዳር 5 /2007 ዓ/ም በገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች እየቀረበ ያለውን ቅስቀሳ እንዳልተቀበሉት የገለፀው መረጃው በተለይ ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ እስካሁን በየደረጃው ለሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል በተከታታይ  እየቀረበ  ያለው ያለፉት ስርዓቶችን የሚወቅስ በዶክመንታሪ ፊልም የተሰነደ ፕሮፖጋንዳ መሰረታዊ ስህተት መሆኑን አስረድተዋል፣፣
    ምሁራኖች እንደገለፁት በየጊዜው ያለፉ የኢትዮጵያ  ስርዓቶችን ፀረ ህዝብ እንደነበሩ የሚተነትኑ ፊልምችና ፅሁፎች እየተዘጋጁ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሚካሄዱ ቅስቀሳዎች የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነትና ህብረት የሚበጥስና የሚበታትን እንጂ የሚያስተሳሰር እንዳልሆነ ከገለፁ በኋላ ይህ ተግባር ደግሞ ገዥው ድርጅት ባለፉት ስርዓቶች ስም እየነገደ የራሱን የስልጣን እድሜ ለማራዘም እየተከተለው ያለው አውዳሚ ተግባር ነው ሲሉ ምሁራኑ እንደገለፁ መረጃው አስረድቷል።