Wednesday, November 5, 2014

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን በሃውዜን ከተማ ነዋሪዎች ላይ እያጋጠመ ያለውን አስተዳደራዊ በደል በመቃወማቸው ብቻ አደናቃፊዎችና የአረና ትግራይ ድርጅት ተላላኪዎች ናችሁ እየተባሉ ሂስ እየተሰነዘረባቸው እንደሆኑ ተገለፀ፣





ነዋሪዎቹ  ለአስተዳድሩ እንዲቃወሙ ያነሳሳቸው  ምክንያት፤ የሃውዜን ከተማ ተጠሪነትዋ ወደ ስንቃጣ ከተማ እንድትሆን ተብሎ፤ ባለፈው ሳምንት በስርአቱ ካድሬዎች በቀረበው ሃሳብ፤ ሃውዜን ከተማ ቀደም ብላ የተመሰረተች ስለሆነች አንቀበለውም ሲሉ መቃወማቸውንና፤ በተለይ ከ 50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ባቀረቡት ጠንካራ ተቃውሞ፤ ሃውዜን በስንቃጣ ስር ሆና ትተዳደር መባሉ፤ ከተማዋ እንዳታድግ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው በማለት ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዳደረጉት ለማወቅ ተችሏል፣  
    በህዝቡ ተቃውሞ የተደናገጡት የህወሃት ማሌሊት የመድረኩ መሪዎች፤ በወቅቱ በግልፅ ቀና ሃሳብ ላቀረቡ ነዋሪዎች፤ እናንተ የአረና ትግራይ ድርጅት ደጋፊዎችና አደናቃፊዎች ናችሁ በማለት፤ በህዝቡ ፊት እንዳስፈራርዋቸው ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታውቋል፣