Wednesday, November 5, 2014

በአዲግራት ከተማ የሚገኙ ካህናት የስርአቱን ካድሬዎች በሃይማኖት ላይ ጣልቃ መግባታቸውን በመቃወማቸው ብቻ እየታሰሩ መሆናቸው ተገለፀ፣





እነኝህ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማ ውስጥ የሚገኙት ካህናት በስርአቱ ካድሬዎች ሃይል እንዲሰበሰቡ እየተገደዱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው፤ መንግስት በሃይማኖት ላይ ለምን ጣልቃ ይገባል በማለት ስብሰባውን ስላልተቀበሉት ብቻ፤ እየታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
    የስብሰባው አላማም በአዲግራት ከተማ ነዋሪ ህዝብ አያስፈልግኑም ተብለው የተወሰነባቸውን ጳጳስ አስመልክቶ እንደሆነና፤ የከተማዋ ካድሬዎች ግን ጳጳሱን እንዲባረሩ ስለማይፈልጉ ካህናቶችን ሰብስበው ለማግባባትና አሳምነው ሃሳባቸውን ለማስቀየር የታሰበ ቢሆንም፤ በካህናቶች ተቀባይነት እንዳላገኘ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣