Wednesday, November 26, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ አምባገነን ስርአት በወለጋ ዞን ጭሮ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት በተማሪዎች መካከል በፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተገለፀ።



    ምንጮቻችን እንደገለፁት በኦሮሚያ ክልል፤ ወለጋ ዞን፤ ጭሮ ከተማ ውስጥ የኢህአዴግ ካድሬዎችና አባላት ውስጥ ለውስጥ በፈጠሩት ከፋፋይ የጎሳ ወሬዎች በተማሪዎቹ መካከል ከባድ ግጭት መነሳቱንና በዚህም ሰበብ ሁለት ተማሪዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
    የኢህአዴግ ገዢ ባለስልጣናት ይህን እኩይ ተግባር እንዲያነሳሱ ያስገደዳቸው ምክንያት ግጭቱን ተቃዋሚዎች እንዳነሳሱት አስመስለው ለማቅረብና ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በተቃዋሚዎቹ ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖራቸው ያለመ እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።