Wednesday, November 26, 2014

የኢህአዴግ ስርዓት የራሱን እኩይ ተግባሮች ለመሸፋፈን ሲል በአዳማ ከተማ እያካሂደው ያለው ያለፉት ስርአቶችን የመውቀስ ፕሮፖጋንዳ የከተማው ማህበረሰብ እንደተቃወመው ተገለፀ።



መረጃው እንደገለፀው ህዳር 10/2007 ዓ/ም የኢህአዴግ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በክልሉ ዋና ከተማ የሚገኘውን ህዝብ በመሰብስብ በህዝቡ ላይ የፈፀመውን ወንጀል ለመሸፈን ሲል ካድሬዎቹን በማሰማራት ያለፍትን ገዢ ስርአቶች በሚውቀስ መንገድ ያካሄደውን የቅስቀሳ ፕሮፖጋንዳ ህብረተሰቡ እንዳልተቀበለውና የስርዓቱን አስመሳይነትም በቀጥታ እንደተቃወመው ለማወቅ ተችሏል።
    የኢህአዴግ ስርዓት ህዝባዊ ሃላፊነት የማይሰማቸውን የኦሆዴድ አባላት ወደ ክልሉ በማሰማራት ታሪካዊ ስህተት እየፈፀመ መሆኑን ባለፉት የዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል።