Saturday, November 15, 2014

የናዕዴር ዓዴት ወረዳ ህዝብ በመብራት ሃይል እጥረት እለታዊ ኑሮውን ለመምራት እንደተቸገረ ተገለፀ፣




    የናዕዴር ዓዴት ወረዳ ህዝብ አጋጥሞት ባለው ተከታታይ የመብራት ኃይል እጥረት ምክንያት፤ ኑሮውን ለመምራት መቸገሩን የገለፀው መረጃው፤ በዚህም ምክንያት- እንደ ምግብ ቤት፤ ሻሂ ቤቶችና ሌሎች ድርጅቶች ከፍተው ሲሰሩ የቆዩ ዜጎች፤ ድርጅታቸውን እንዲዘጉ መገደዳቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣
    በመብራት ሃይል መቋረጥ ምክንያት ችግር ላይ ከወደቁ አካባቢዎች ውስጥ ዕዳጋ ሰሉስ፤ ዳዕሮ ሓፋሽና ሌሎች ታዳጊ ከተማዎች እንደሆኑ የገለጸው መረጃው፤ ህዝቡ ባጋጠመው የመብራት ሃይል ችግር ምክንያት ተማርሮ በአካባቢው ወደ ሚገኙ አስተዳዳሪዎች ብሶቱን ቢያቀርብም፤ መፍትሄ የሚሰጠው አካል እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል፣
    ይህ በንዲህ እንዳለ የናዕዴር ዓዴት ወረዳ ህዝብ በንጹህ ውሃ እጥረት እየተሰቃየ እንዳለና ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ በመጠቀሙ የተነሳም፤ በውሃ ወለድ በሽታዎች ለረጅም ጊዜ ተጋልጦ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣