Tuesday, November 18, 2014

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ የአረና ትግራይ ድርጅት አባላት። በገዢው ስርአት እናንተ አረና አይደላችሁም የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላችሁ እየተባሉ። በፌደራል ፖሊስ ተይዘው እየታሰሩ መሆናቸው ተገለፀ፣




    በመረጃው መሰረት። እነዚህ በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ የአረና ትግራይ ፓርቲ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት። በጉጅሌው የኢህአዴግ ስርአት ፖሊሶች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። የታሰሩበት ምክንያትም የተቃዋሚው ድርጅት አባላት በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እያገኙ በመሄዳቸውና ስርዓቱ በመጪው ምርጫ ላይ እንዳያሸንፉ ስጋት ላይ ስለ ወደቀ መሆኑን ያገኘነው መረጃ አስታወቀ፣
    በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ከታሰሩት የአረና ተቃዋሚ ድርጅት አባላት አንዱ። አቶ አማረ የተባሉ ዜጋ ሲሆኑ። ግለሰቡ ለምንድን ነው የታሰርኩት ብለው በጠየቁበት ሰዓት። አንተ የአረና ተቃዋሚ ድርጅት አባል ሳትሆን። የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር እየተገናኘህ ስለምትሰራ ነው የሚል ምክንያት መሰጠታቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣