Tuesday, November 18, 2014

በአብራ-ጂራና ዳንሻ አካባቢ የሚገኙ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚያካሂዱ ድርጂቶች የመታገያ አላማቸውን ለህዝብ ስላሳወቁ ብቻ እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስረዱ፣




     ከተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል አንድነትና አረና ጥቅምት 24 /2007 ዓ/ም ወደ አብራ-ጂራና ዳንሻ አካባቢዎች በመሄድ ህዝብ ሰብስበው ቅስቀሳ ለማካሄድ በሞከሩበት ጊዜ በገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ,ግ ስርዓት እንደታሰሩ የገለፀው መረጃው። ከታሰሩት የተቃዋሚ ድርጅቶች መካከልም  የአረና ድርጅት አባል የሆኑ አቶ አንዳው ተገኝ፤ አቶ እንግዳው ዋኘውና አቶ አባይ ዘውዱ የተባሉት እንደሚገኙበት ገልፀዋል፣
  መረጃው ጨምሮም ይህን ህጋዊነት የሌለው ተግባር ይታዘብ የነበረው ህዝብ በበኩሉ ለምን ታሰሩ? የሚል በተኩስ የታጀበ ከፍተኛ ተቃውሞ ስላካሄደ ለጊዜው ከእስራት የተለቀቁ ቢሆንም ህዝቡ ወደየ መኖሪያ ቤቱ ከተበተነ በኋላ ግን የፌዴራል ፖሊሶች አፍነው እንደወሰዷቸው ምንጮቻችን አስረድተዋል፣
  በተመሳሳይ። በጎንደር ዳንሻ መስመር ልዩ ስሙ ሰሮቋ በተባለ አካባቢ ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ 8 ወገኖቻችን በፌድራል ፖሊስ ታፍነው እንደተወሰዱ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣