በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ በአዲ ነብርኢድ
ከተማ የሚገኙ ደህንነትና የህወሃት ካድሬዎች ከፖሊስ ጋር በመተባበር በግልና በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርተው ኑሮአቸውን የሚመሩ
የህወሃት አባላት ያልሆኑትን ዜጎቻችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂደውን የትህዴን ድርጅት ስለምትደግፉና ስለምትተባበሩ ነው በምናካሂደው
ስብሰባ ላይ የማትሳተፉት በሚል ምክንያት በርካታ ሰዎችን በተለየ ሁኔታ አስረው በማሰቃየት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።
የህወሃት ካድሬዎችና የደህንነት አባላት ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን በመቀጠል
በከተማው ውስጥ በማረት ተቀጥሮ ሲሰራ የቆየውን አቶ አርአያ ሓጎስ የተባለውን ንፁህ ወገን የትህዴን አባል ነህ በሚል ሰንካላ ምክንያት
ታህሳስ 5/2007 ዓ/ም በፖሊስ አስይዘው በላዩ ላይ ከባድ ድብደባ ስለፈፀሙበት በህዝብ ፊት ቀርቦ ሳይወድ ትህዴን ነኝ ለማለት
እንደተገደደና እስካሁንም በልዩ ሁኔታ ታስሮ እየተደበደበ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።