Saturday, December 27, 2014

በትግራይ ክልል የሚገኙ የፍትህ አካላት በህዝቡ ላይ እያደረሱት ያለው ግፍ እየከፋ በመሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።



በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት የፍትህ አካላት የሆኑ የህወሃት ካድሬዎች ጉቦና ሌሎችንም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ለማግኘት ሲሉ ባለ ጉዳዮችን ከ7 እስከ 8 ወራት ያህል በቀጠሮ እየሸኙና እለታዊ ስራቸውን በማስተጓጎል ወደ ፍርድ ቤት እንዲመላለሱ ማድረጋቸውን  መረጃው አስታውቋል።
    የህዝብ ኃላፊነት የማይሰማቸው የፍትህ አካላት ፍትህን ፍለጋ ወደ መስርያ ቤታቸው ለሚመላለሰው ህዝብ ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ቀጠሮ እየሰጡ ማህበራዊ ኑሮውን እንዳይመራ ከፍተኛ ጫና እያደረሱበት መሆናቸውንና ገንዘብ ያለው ወገን ከዚሁ ችግር ለመዳን ሲል ሳይወድ ጉቦ ሲከፍል ይህን ማድረግ ያልቻለው ወገን ደግሞ ወደ ፍርድ ቤት በመላለስ ጊዜውን በከንቱ እያሳለፈው መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።