Saturday, January 17, 2015

በተለያዩ የመከላከያ ሰራዊት ክፍል ውስጥ ያሉ የስርዓቱ ነባር ታጋዮች የስርአቱ ደህንነት ስላሳሰባቸው ከውትድርና እንዲሰናበቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለፀ።



    በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደ ገለፁት የስራ መልቀቅያ እያቀረቡ ያሉት የሰራዊቱ አባላት ከህወሃት ትጥቅ ትግል ጀምረው በተለያዩ የሃላፊነት እርከን ላይ ተመድበው እየሰሩ መቆየታቸውንና ስርዓቱ ውስጡ ቀስ በቀስ እየበሰበሰና በሰው ኃይል እየተመናመነ ስለሚገኝ በአጭር ቀን ፈራርሶ መውደቁ አይቀረውም የሚል እምነት በመያዛቸውና ከአደጋው አስቀድመው ለመልቀቅ በሚል የስራ መልቀቂያ እየጠየቁ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    መረጃው በማስከተል በአየር ኃይል ስታፍ ውስጥ ተመድበው ሲሰሩ የቆዩትን የትግራይ ተወላጆች እየታየ ያለውን አውሮፕላን ይዞ የማምለጥና ስርአቱን የመክዳት ሁኔታ በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ የመነጋገርያ አርእስት ሆኖ ስለሚገኝ የድሮ ታጋዮቹ እየጠየቁት ያለውን የስንብት ጥያቄ አሁን እያጋጠመ ካለው አጋጣሚ ራሳቸውን ለማግለል እንደሆነ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።