Saturday, January 17, 2015

በትልቅ ስጋትና ውጥረት ላይ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች ከውጭ የሚመጣ ጠላት እንዳለ በማስመሰል የህዝቡን አስተሳሰብ ለመቀየር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ተገለፀ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ሃላፊነት በጎደለው አሰራራቸው ምክንያት በህዝቡ ያጡትን ተቀባይነት ለመመለስ ሲሉ በጥልቅ ጭንቀት ውስጥ ተጠምደው እንደሚገኙ የገለጸው መረጃው ይህን ለማድረግ እየተጠቀሙበት ካለው መንገድም በወረዳው የሚገኙትን ታጣቂ ሚሊሻዎች በመሰብሰብ ከውጭ የሚመጣ ጠላት ስላለ እሱን ለመመከት በሚል ተከታታይ ወታደራዊ ስልጠና እየሰጧቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው የስርዓቱ ካድሬዎች በወረዳዋ ያሉትን ታጣቂ ሚሊሻዎች ከህዝቡ ጋር አንድነት ፈጥረው በላያቸው ላይ ተቃውሞ እንዳያስነሳ ከዚህ በፊት በቀበሌ ከፋፍለው ታማኝና የማይታመኑ በማለት ሲከፋፍሏቸው የቆዩ መሆናቸውን የሚታወቅ ሲሆን አሁንም ዋላኹና ዕልሚ በተባለው አካባቢ በመከላከያ የስለያ አባላት በኩል ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑንና ዋናው ዓላማም በስልጠናው መጨረሻ ላይ የሚባረር አባርረው ታማኝ የሚባሉትን ለመያዝ ያለመ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።