Thursday, January 1, 2015

በሽራሮ ከተማ የሚኖር ህዝብ በንፁህ የሚጠጣ ውሃ እጥረት ምክንያት እለታዊ ኑሮውን መምራት ተቸግሮ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ።




   በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽራሮ ከተማ የሚኖረው ማህበረሰብ አጋጥሞት ላለው የንፁህ ውሃ እጥረት ስልጣን ላይ ያሉት አስተዳደሮች መፍትሄ እንዲያደርጉለት ቢጠይቅም በከተማዋ አስተዳደር በኩል ግን መንግስት የንፁህ ውሃ ችግር እንዳለ ቢያውቅም እንኳን በመንግስት በጀት ዉሃ ማስገባት ግን ፕሮግራም የለውም። አሁንም ቢሆን ንፁህ የሚጠጣ ውሃ ማግኘት ከፈለጋችሁ  እያንዳንዱ መንደር  ያዋጣውን 40 ሽህ ብር በቂ አይደለም በሚል ሰበብ አንድ ሰው ከ200 በቶ ብር በላይ ማውጣት አለበት በማለት አስገድደው በማስከፈል ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
  መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ህብረተሰቡ በህብረት እና በግል ለንፁህ ውሃ መስርያ በማለት የተጠየቀውን ገንዘብ አዋጥቶ እያለ እንደገና ለውሃው መተላለፍያ የሚሆን መስመር መስርያ በነፃ ቆፍሩ እያሉ የተዋጣውን ገንዘብ  ለማሽንና ለአበል እያሉ ለግል ኪሳቸው መሙያ በማድረግ ድሃውን ህዝብ ግን መዳበ ወደ ተባለ ቦታ ወስደው በነፃ እያሰሩት እንደሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ገልጿል።