በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በህዝባዊ ተቃውሞ ሰግቶ የሚገኘው የኢህአደግ ገዢ
ጉጅሌ በየአከባቢው የሚገኙ መንገዶች የታጠቁ አባላትን በማሰማራት ዜጎችን እያሰቃዩ እንዳሉ ከገለፀ በኋላ በዚህ መሰረትም በሸራሮና
ዓዲ-ጎሹ መሸጋገሪያ ድልድይ ላይ የሚገኙ የፍተሻ ኬላው ጠባቂ የሆኑት የስርአቱ ተላላኪዎች አንድ ለግዜው ስሙ ያልታወቀ ወጣት መታወቂያ
አልያዝክም ብለው ተሳፍሮባት ከነበረው መኪና አውርደው በማስቀረት ሌሊት ሊጠፋ መክሯል በሚል ሰንካላ ምክንያት በጥይት ተኩሰው እንደገደሉት
ተገለጸ።
ይህ ንፁህ ዜጋ
በታጠቁት የኢህአደግ አምባገነን ስርአት በጥይት ተመትቶ ሸራሮ ከተማ ወደ ሚገኘው ህክምና የተወሰደ ቢሆንም የደረሰው አደጋ ከባድ
ስለነበር ወድያውኑ ህይወቱ ማለፉና በአሁኑ ግዜ በሃገራችን ያለመታወቂያ ካርድ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ ወንጀል መሆኑን መረጃው
ጨምሮ አስረድቷል።