Monday, January 12, 2015

በሶማሌ ክልል የሚገኙ የስርአቱ ሚሊሻዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እየተገደሉ መሆናቸው ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በሶማሌ ክልል  ፊቅ ዞን ከተማ ድንዱማት በተባለው አካባቢ የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት ሚሊሻዎች ታህሳስ 22/2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተግድለው እንደተገኙ የገለፀው መረጃው ገዳዮችም የኦጋዴን  ነፃ አውጪ  ግንባር /ኦብነግ/ ሳይሆን አይቀርም በማለት የአካባቢው ህዝብ እየተናገረ መሆኑን የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    በዚሁ ሁኔታ ስጋት ላይ የወደቁ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ከ40 ኪ/ሜትር በማይበልጥ ርቀት ላይ የጥበቃ ኬላዎችን ማቆማቸውንና በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን ነዋሪ ህዝብም የመታወቂያ  ወረቀት በመጠየቅ እያንገላቱትና ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ማህበራዊ ኑሮውን እንዳይመራ ችግር እየፈጠሩበት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።