በአየር ሃይሉ ውስጥ ያሉ ምንጮቻችን እንደገለፁት
ባለፈው ቅርብ ቀናት ከሃዲውን የኢህአዴግ ስርአት በመቃወም ከኢትዮጵያ አየር ኃይል አንድ የውግያ ሄሊኮፕተር የያዙ 2 ፓይለቶችና፤
አንድ ቴክኒሻንና ከነሱ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ከንያ የጠፉት 4ፓሎተወች መጥፋታቸውን ተከትሎ ጄነራል ሳሞራ የኑስ ወደ ቦታው በመሄድ
ስብሰባ ማካሄዱንና ጭብጥ መረጃ በሌለው በጥርጣሬ ብቻ ተነሳስቶ ከኮበለሉት ጋር ግንኝነት አላችሁ በማለት ኦፊሰሮችንና ሰራተኞችን
ሲያሰፈራራቸውና ሲያስራቸው እንደሰነበተ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
እነዚህ የአየር ሃይሉ አባላት ሄሊኮፕተሩን ይዘው ከኮበለሉ በኋላ በኢትዮጵያ
አየር ኃይል ውስጥ ትልቅ ውጥረት ማስከተሉንና ማንኛውም አውሮፕላን ለልምምድ ይሁን ለሌላ ስራ መብረር እነደሌለበት ጥብቅ መመሪያ
መሰጠቱን የገለጸው መረጃው ባለስልጣኖቹ እየተቀያየሩ በየዕለቱ ስብሰባዎችን በማካሄድ ላይ ቢሆኑም አሁንም ውጥረቱ እየቀጠለ መሆኑን
መረጃው አክሎ አስረድቷል።