Wednesday, February 11, 2015

በከፍተኛ የኢህአደግ ስርአት መከላከያ ጀነራል አዛዦች ያለመተማመን የወለደው ሃይለኛ ጭቅጭቅ ላይ እንዳለ ከመከላከያ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በከፍተኛ የኢህአደግ መከላከያ ሰራዊት ጀነራል አዛዦች ያለመስማማት ተፈጥሮ እንዳለ  ከገለፀ በኋላ በተለይ ደግሞ የአየር ሃይል አዛዥ ሃላፊ የነበር ሜጄር ጀነራል ሞላ ሃይለማሪያም ከሃላፊነቱ ተወግዶ በመከላከያ ሰራዊት ኢንስፔክሽን ጉጅሌ እየሰራ ባለበት በአሁኑ ግዜ በአሁኑ ሰአት ተፈጥሮ ያለውን የመበታተን አደጋ መንስኤው አንተ ስለሆንክ  ተጠያቂ  ነህ ሲሉት ሊቀበላቸው እንዳልቻለና በዚህ የተነሳም በሃይለኛ መሳሳብ ላይ እንዳሉ ታውቋል። 
መረጃው ጨምሮ ሜጄር ጀነራል ሞላ የቀረበለትን ሃሳብ ሳይቀበል መነሻው በአየር ሃይል ተከስቶ ያለው ችግር እኔ በነበርኩበት ግዜ ሳይሆን አሁን ያለው ብልሹ አሰራር የፈጠረው ነው በማለት ለሰጠው ምላሽ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ስላልተዋጠለት በሁለቱም ከፍተኛ አዛዦች መካከል መቃቃር ተፈጥሮ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።