Wednesday, February 11, 2015

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች የመከላከያ ሰራዊት አባሉን የምርጫ ካርድ ወስደው ድርጅቱን እንዲመርጡ ያቀረቡት ቅስቀሳ ተቃውሞ እያጋጠመው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።



በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን እንድገለፁት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ይህ በተለያየ ቦታ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አባል የምርጫ ካርድ ወስዶ ገዥውን መንግስት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ,ን መምረጥ አለበት በማለት ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የቆዩ ሲሆን ሰራዊቱ ግን እኛ የህዝብና የሃገር ጠባቂዎች እንጂ ከፖለቲካዊ ድርጅቶች ነፃ መሆን ሲገባን ለምን ምረጡ እያላችሁ ታስቸግሩናላችሁ ሆኖም ግን ከመረጥን ሌሎችን ድርጅቶችን እንመርጣለን እንጂ ስለምን እናንተን ብቻ እንድንመርጥ አታስገድዱን  እንዳሉ ታውቋል።
በመከላከያ ስራዊት የሚካሄደው ምርጫ የክፍለ ሰራዊት የፖለቲካ ሃላፊዎችና ከፍተኛ አዛዦች የሚከታተሉት ሲሆን ምርጫ የሚካሄድባቸው ጣቢያዎች ደግሞ በሬጂመንት እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።