Friday, February 13, 2015

በአክሱም ከተማ የሚገኘው የቅድስተ ማርያም ሆስፒታል ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም በማለት የከተማዋ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



 በመረጃው መሰረት በትግራይ ማዕክላዊ ዞን በአክሱም ከተማ የሚገኘው መንግስታዊ ሆስፒታል  በተቋሙ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የሚሸጥ መድሃኒት እያለ ህመምተኞች ወደ ግል ፋርማሲ በመሄድ የታዘዘላቸውን መድሃኒት በእጥፍ ዋጋ እንዲገዙ በዶክተሮች ስለሚታዘዙ የታዘዘላቸውን መድሃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ደግሞ  ስለሌላቸው ለሞትና ለስቃይ ተጋልጠው እንደሚገኙ ከገለፁ በኋላ ጥር 24/2007 ዓ.ም የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ሚመለከተው አካል በመሄድ አቤቱታቸውን እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው አክሎ ይህንን ከስነ-ምግባር ውጭ የሆነ ስራ እየፈፀሙ ካሉት ውስጥ ዶክተር መስፍን አንዱ እንደሆኑ ለህመምተኞች መርምረው መድሃኒት እንዲገዙ ወደ ግል ፋርማሲያቸው ሲልኳቸው የታዘቡ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን በመግለፅ ላይ ያሉ ሲሆን በግልፅ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ካሉ ዜጎቻችን ውስጥ ደግሞ ሻምበል ክፍሎም አፅበሃ፤ ሻምበል ማዕረግና ሌሎችም እንደሆኑ ታውቋል።