እንደምንጮቻችን ዘገባ ከ13 አመት በፊት ምርታማነትን
ለመጨመር በሚል በቅናሽ ዋጋ የተሸጡ የተለያዩ ግብዓቶችን ከመጪው
ምርጫ በፊት በአዲስ ሂሳብ መሰራት አለባቸው በሚል በመጪው ምርጫ ኢ.ህ.አዴ.ግ.ን ሊመርጡ አይችሉም የሚባሉ ዜጎችን ከፍተኛ ገንዘብ
እንዲከፍሉ እያስገደዷቸው ሲሆን። ነዋሪዎቹን ለከፍተኛ ችግር ከሚያጋልጡት የገዥው መንግስት ተላላኪዎች መካከል ኢንስፔክተር ባደግ የወረዳው የፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ፤
ሮቤል የፍትህ ፅህፈት ቤት ሃላፊ፤ ግሩም የወረዳው የብአዴን ፅህፈት ቤት ሃላፊና ሌሎችም የሚገኙ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው በማከል
በህገወጥ መንገድ 20.4 ሚሊዮን ብር ከደቅ ዘረገነት ቀጠና 12 ሚሊዮን ብር ከወርቅ ሜዳ ቀጠና የተሰበሰበ ሲሆን በችግሩ ሰለባ
መሆናቸውን ከገለፁት መካከልም አቶ ሁነኛው አምበሌ፥ አቶ የሽዋስ ስዩም፥ አቶ ታሪኩ ፍቃዴና ቄስ አበበ የተባሉት የወረዳው ነዋሪዎች
በመንግስት ጫና ለድህነት ተጋልጠናል ሲሉ ብሶታቸውን ገልፀዋል፣