Tuesday, April 28, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ።



እንደምንጮቻችን መረጃ የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት በመንግስታችን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሊያደርግ ሰራዊቱን በሁመራና አካባቢው ላይ አስጠግቷል በሚል ፍርሃት የወለደው ስብሰባ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
   እኒህ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው መንግስት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወስድ ስለሆነ በክልላችን ስለድርጅቱ የሆነ መረጃ ያመጣ ሰው ለማበረታቻ የሚሆን ሽልማት ይሰጠዋል በማለት ህብረተሰቡን በማታለል ስራ ላይ ተጠምደው እንደሰነበቱ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።