Tuesday, April 28, 2015

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚኖሩ ዜጎች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎችና ተባባሪዎች ናችሁ እየተባሉ በመታሰር ላይ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ የሚኖሩ ንፁሃን ዜጎች በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ሰላማዊ የተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ልዩ ግንኙነት አላችሁ ተባባሪዎችና ደጋፊዎችም ናችሁ  በማለት ምንም የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው ከሚሰሩበት ቦታ እየተያዙ በአስተዳዳሪዎች እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው የሚገኙ የገዥው ስርዓት ካድሬዎችና አስተዳዳሪዎች በአሁኑ ጊዜ የአካባቢውን ማህበረሰብ እየሰበሰቡ ድርጅታችን ብ.አ.ዴ.ን/.ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፍፁማዊ መሆኑን አውቃችሁ ከድርጅታችን ውጪ እንዳትቀበሉ እያሉ በቀሰቀሱበት ጊዜ የስርዓቱን ደካማ ጎኖች በማንሳት የተቃወሙትን ሰዎች የስርዓቱ ካድሬዎች ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ናችው ያሏቸውን 7 ዜጎች ያለምንም ወንጀል አስረው እያሰቃዩዋቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።