Saturday, April 25, 2015

በአማራ ክልል አዊ ዞን ዳንግላ ከተማ የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አገዴፓ) በርካታ ህዝብ የተገኘበት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዱ ተገለፀ፣



    በደረሰን መረጃ መስረት። በአማራ ክልል አዊ ዞን ዳንግላ ከተማን ጨምሮ  ጫራና ጨረቃ በተባሉ ሁለት ከተሞች ሚያዝያ 1 ቀን 2007 ዓ/ም የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አገዴፓ) በርካታ ህዝብ የተገኘበት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዱና በቅርቡም ጓንጓ ወረዳ ዲንካራና ቅዳማጃ በተባሉ ሁለት ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ዝግጅቱን ጨርሶ  ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑ ታውቋል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ  አምባገነኑ ገዥው የኢህ.አ.ዴ.ግ መንግስት  በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን ገንዘብ እየከፈለ በአዴንን ደግፈው ለሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ እያደረገ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ሰልፉን ለሚያጅቡ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ እየተሞላላቸው እንዲያጅቡ እየተገደዱ መሆናቸውን አንዳንድ በባህርዳር ከተማ  የሚገኙ ወገኖች ተናግረዋል፣
    በተመሳሳይ የተቃዋሚ ድርጅቶች በአንዳንድ ወረዳዎች የማስታወቂያ ቦርዶች ላይ የለጠፏቸውን ፕሮግራሞችና ምልክቶችን የታጠቁ ሃይሎች እየገነጠሉ የጣሏቸው ሲሆን ለምን ትቀዳላችሁ የሚል ጥያቄ ላነሱ ተቃዋሚዎችም ለሰዓታት እያሰሩ ዳግም ላይለጥፉ እያስፈረሙ እንደለቀቋቸው ከወልዲያ ከተማ አዳጎ አዳራሽ ማስታወቂያ ቦርድ ላይ የተገነጠለውን የኢዴፓ በራሪ ወረቀት ዋቢ በማድረግ  ምንጮቻችን ገልፀዋል፣