Saturday, April 25, 2015

በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች የግብርና ስራዎችን አስመልክቶ የክረምት የሰብል ስራና አመለካከት በሚል አጀንዳ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸው ተገለፀ፣



በክልሉ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ከየወረዳው ለተወጣጡ 200 አርሶ አደሮች ለተከታታይ 8 ቀናት ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን የዚህ ስልጠና ዋና አጀንዳም የግብርና ስራዎችን አስመልክቶ የክረምት የሰብል ስራና አመለካከት በሚል ይሁን እንጂ በአጠቃላይ መጪውን ምርጫ በተመለከተ ብ.አ.ዴ.ንን መምረጥ እንዳለባቸውና ከአርሶ አደሮች በኩልም ከዚህ በፊት በማህበራት በግላችን ይሸጥ የነበረው ማዳበሪያ አሁን ፍትሃዊነት በጎደለው ሁኔታ በአብቁተ 1ለ7 በሚል  አደረጃጀት በህብረት እንድንገዛ መደረጉ እየጎዳን ነው ሲሉ መቃወማቸው ታውቋል፣