Wednesday, April 22, 2015

የሁመራ ከተማ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ነዋሪውን ህዝብ በየግሉ እየያዙ ለመጪው ምርጫ እንዴት ተዘጋጅተሃል ምንስ እቅድ አለህ በማለት እያስጨነቁት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ የሚገኙ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች በከተማዋ ዕለታዊ ስራውን ለማሳለጥ የሚንቀሳቀሰውን ህዝብ በየቤቱ እየዞሩ ምን እቅድ አለህ ለመጪው ምርጫስ እንዴት ተዘጋጅተሃል እያሉ በጥያቄ እያስጨነቁት መሆናቸውን አስረድተዋል፣
    የከተማዋ ህብረተሰብ በበኩሉ በእንደዚህ አይነት ስራ ላይ የተሰማሩ ካድሬዎችን። ምን ስለፈለጋችሁ ነው በሰላም ሰርተን ኑሮአችንን እንዳንመራ በጥያቄ አዕምሮአችንን የምታስጨንቁት። የሚያሰጋችሁ ነገር ካለ በግልፅ ተናገሩ ካልሆነ ግን ሱሪያችንን በአንገታችን እንድናወጣ አይነት ጥያቄ እየጠየቃችሁ አታስቸግሩን ውስጣዊ ጭንቀታችሁ ለራሳችሁ እንጂ ህዝባችንን አይወክልም በማለት። ጥላቻን የሚያንፀባርቅ ምላሽ እንደሰጧቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣