Monday, April 20, 2015

በማዕከላዊና በምዕራብ እዝ የሚገኙ ከፍተኛ የእስታፍ አዛዦችና አባላት ትህዴን በላያችን ላይ ጥቃት ለማድረግ አዲስ ዝግጅት እያደረገ ስለሆነ ምሽጋችሁን አጠናክሩ የሚል ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ተገለፀ፣



  ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን እያሳየው ያለው ቀልጣፋ እድገትና ጥንካሬ ለህልውናቸው አስጊ እየሆነ በመምጣቱ ምክንያት። በማዕከላዊና በምዕራብ እዝ የሚገኙ ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮችና የእስታፍ አባላት ትህዴን በአዲስ አደረጃጀት ተጠናክሮ በላያችን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት እያደረገ ስለሚገኝ ምሽጋችሁን አጠናክራችሁ በትኩረት ዙሪያውን ጠብቁ የሚል ትእዛዝ መጋቢት 26/207 ዓ.ም በከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፣
   ከእዞቹ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚገልፀው።- ከፍተኛ የኢህአዴግ ቡድን የሰራዊት አመራሮች ባስተላለፉት ፍርሃት የወለደው ትእዛዝ ምክንያት። በሰራዊቱ መካከል ሃይለኛ የሆነ ስጋትና ሽበራ ሰፍኖ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ገልጿል፣