በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ በርካታ ተማሪዎች የተሳተፉበት ተቃውሞ። መጋቢት
29/2007 ዓ/ም መካሄዱን የገለፀው መረጃው። በትምህርት ቤቱ ውስጥ የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁሶችና የማህበራዊ አቅርቦት እጥረት
በከፍተኛ ደረጃ እነደተከሰተና በዚህም ምክንያት ሰልፈኞቹ በትምህርት ቤቱ ግቢ የጀመሩትን የተቃውሞ ሰልፍ። ከዩኒቨርሲቲው ቕጥር ግቢ ውጭ በመውጣት ሊቀጥሉ በመኮሩበት ሰዓት ብዛት ያላቸው
የፌደራል ፖሊስ አባላት ግቢውን በመዝጋትና ዙርያውን በመክበብ በዱላ እየደበደቡ እንዳገቷቸው ለማወቅ ተችሏል፣
ተማሪዎቹ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ካሰሙት መፈክር ውስጥ።
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተለያዩ ችግሮችና ረሃብ በዝቶዋል፤ ተማሪው ወላጆቹ በሚልኩለት ገንዘብ ነው እየተመገበ ያለው፤ በተማሪው ስም
የሚመደበው በጀት የት እየዋለ ነው፤ ለዩኒቨርሲቲው የሚመጥን የትምህርት መሳርያ አቅርቦት የለም፤ ለስሙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንባላለን
እንጂ በቂ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት አይሰጠንም፤ አስተማሪዎችም በብቃታቸው ሳይሆን የኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች በመሆናቸው
ብቻ ስለሚመደቡ ደካሞች ናቸው የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን እያሰሙ እንደነበሩ ተገልጿል፣
በተነሳው ተቃውሞው
የተደናገጠው የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንትና ዶ/ር ክንደእያ
ገብረሂወት። ተማሪዎቹን ሰብስቦ የተነሳውን መሰረታዊ ጥያቄ ወደ ጎን በመተው አታልሎ ሁኔታውን ሊያበርደው ቢሞክርም። ተማሪዎቹ ባስነሱት ጥያቄ ላይ ፅኑ አቋም በማሳየታቸው ግን ሳይግባቡ መለያየታቸውን
መረጃው አክሎ አስረድቷል፣