Wednesday, April 29, 2015

በአማራ ክልል፤ ሰሜን ሽዋ ዞን ልዩ ስሙ መራኛ በተባለው አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ተቃዋሚ ድርጅቶችን ደግፋችኃል በሚል የእርሻ መሬታቸውን እየተነጠቁና እየታሰሩ መሆናቸውን ተገለፀ።



   በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን የመራኛ አካባቢ ነዋሪዎች የሆኑ ዜጎቻችን ከገዢው የኢህአዴግ ስርዓት ውጭ ተቃዋሚዎችን ደግፋችኃል በሚል ምክንያት ከ 46 በላይ የሚሆኑ አርሶ-አደሮች በህጋዊ መንገድ ተሰጥቷቸው የተለያዩ ፍራፍሬዎችና የሸንኮር አገዳ ተክል ተክለው ሲጠቀሙበት የቆዩትን መሬት በአስተዳዳሪዎቹ በመነጠቃቸው ምክንያት የመድረቅ አደጋ እንደደረሰበት የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
    ተቃዋሚ ድርጅቶችን ደግፋችኃል ተብለውና ከፍተኛ ጉልበትና ገንዘብ ወጪ አድርገው ያሳደጓቸውን ቋሚ ተክሎች ከተነጠቁ ሰዎች መካከል አቶ ዳርጊ፤ አቶ ደጀኔ ወ/ሮ ፋጢ ይመር የተባሉ እንደሚገኙባቸውና የቀሩትም በእስርቤት ታጉረው እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስታውቋል።