Wednesday, April 29, 2015

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የኮረም ከተማ ነዋሪዎች ከብቶቻቸውን የሚያሰማሩበት የግጦሽ መሬት በኢህአዴግ ስርዓት ስለተከለከለ ከአስተዳዳሪዎቹ ጋር መጋጨታቸው ተገለፀ።



የኮረም አካባቢ ነዋሪዎች የተከለከለውን ቦታ ለረጅም አመታት እንስሳዎቻቸውን በማሰማራት ለግጦሽ ሲጠቀሙበት የቆዩትን መሬት በአሁኑ ጊዜ ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ከብቶቻችሁን ወደ ቦታው እንዳታሰማሩ ብሎ ስለከለከላቸውና በከፍተኛ ችግር ላይ ስለሚገኙ አርሶ አደሮቹና አስተዳዳሪዎቹ በከባድ ጥል እንደሚገኙና እስካሁንም ሁኔታው መፍትሄ እንዳላገኘ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።
   መረጃው ጨምሮ የአካባቢው አርሶ አደሮች ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ለራሱ ጥቅም ሲል መስዋእት እንድንከፍል ብቻ እንጂ የህዝቡን ጥያቄ አዳምጦ መፍትሄ የሚሰጥ አይደለም በማለት ስርዓቱ እየተከተለው ያለው ህዝቡን መሰረት ያላደረገ እርምጃ እንዳልተቀበሉት መረጃው አክሎ አስረድቷል።