በአማራ ክልል የሚገኙ የብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች
በውስጥና በውጭ አገር ሆነው ስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት የሚታገሉትን
ተቃዋሚዎች እያገዛችሁ ነው በማለት በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችንና የመንግስት ሰራተኞችን እንዲሁም አርሶ አደሮችን በማሰርና
በማስፈራራት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢህአዴግ ስርዓት በህዝቡ ተቃውሞ እጅግ ተደናግጦ
ስለሚገኝ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማን ከማን ተገናኘና አብሮ ዋለ በሚል እኩይ ተግባር ንፁኃን ሰዎችን እያንገላታ እንደሚገኝ
መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።