Wednesday, April 22, 2015

የትግራይ ባለስልጣናት በሃውዜን ወረዳ ያካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ተገለፀ፣



    የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ኪሮስ ቢተውና ጎበዛይ ወለአረጋይ መጋቢት 28/2007 ዓ.ም ለሃውዜን ወረዳ ህዝብ ስብሰባ እንዳካሄዱላቸው የተገለፀ ሲሆን። የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳም ወጣቱ ወደ ወትድርና አንገባም ስለላ። እናንተ መክራችሁ እንዲገባ አድርጉት የሚል መሆኑንና። በስብሰባው ላይም ለሃውዜን ህዝብ እንደቀድሞ አይደላችሁም፤ በህወሃት ሃላፊዎች በሚደረጉ መድረኮች ሁሉ  ተቃውሞ ታሰማላችሁ የሚሉና ሌሎችንም የያዘ አጀንዳ እንደነበር የገለፀው መረጃው። የተካሄደው ስብሰባም በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንደጣና ያለምንም ፍሬ እንደተበተነ ታውቋል፣
    የስብሰባውን አጀንዳ የሰሙት የሃውዜን ነዋሪዎች በበኩልቸው የህወሃት መሪዎች ለህዝብ የምታስቡ  አይደላችሁም። አይደለም አሁን ልጆቻችንን ወደ ውትድርና ልትመለምሏቸው ይቅርና። እኛ እስካሁን ድረስ ያገለገልናችሁም መሮናል። ስለዚህ ምንም ለውጥ ስለሌላችሁ የያዛችሁት ስልጣን ይበቃችኋል የሚል ተቃውሞ በማስነሳት እንደመለሱላቸው ለማወቅ ተችሏል፣
    ተሰብሳቢዎቹ አክለው።- ልጃችን ኮለኔል ሃዋዝ ወልዱ ከ69 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሃት ጋር በርካታ የጀግንነት ስራዎችን ቢፈፅምም። አሁን አካሉን ከጎደለ በኋላ የታለ ብላችሁ ማየት ስለተሳናችሁ የቤተሰቦቹ ሸክም ሁኖ ይገኛል። ይህንን እያየን ዳግመኛ ልጆቻችን መስጠቱስ ይቅርና ከናንተ ጋር ያሉት ወታደሮችም እኛን ሰምተው ጥለዋችሁ ቢሄዱ መልካም ተግባር ነበር በማለት የተቃወሟቸው ሲሆን። የነበረው ስብሰባም ያለምንም ስምምነት እንደተበተነ ያገኘነው መረጃ አመለከተ፣



ዜና