የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት ባልተሰተካከለ
የአስተዳደር ችግር ምክንያት። በህወሃት አስተዳደር ላይ እያነሳ ያለው ተቃውሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠነከረ በመምጣቱ የተነሳ። የህወሃት
ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመጋቢት 26 እስከ 27 /2007 ዓ.ም ስብሰባ እንዳካሄደ መረጃው የገለፀ ሲሆን። የስብሰባው ዋና አጀንዳም።
ህዝቡ እኛን ትቶ ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየገባ ስለሆነ። ከ14 አመት በፊት ከማዕከላዊ ኮሚቴ ተባርረው ለነበሩ ሰዎችና ለስርዓቱ
ሲቃወሙ ከቆዩት ጋር ድርድር መጀመር አለብን የሚል አጀንዳ የያዘ ሲሆን። በዚህ የተነሳም ማዕከላዊ ኮሚቴው በሶስት ቡድን እንደተከፈለ
ለማወቅ ተችሏል፣
አባይ ፀሃየ የያዛቸውን ብዱን ለብዙ አመታት ተባርረው ከቆዩ ነባር የህወሃት
ማዕከላዊ ኮሚቴዎች ጋር አሁን መደራደር አንችልም የሚል ሲሆን። እነ ሰብሃት ነጋና አባይ ወልዱ የያዟቸው ደግሞ አሁን የህዝቡ ተቃውሞ
እየተባባሰ በመጣበት ሰዓት አማራጫችን ከነሱ ጋር ተደራድሮ መስማማት ብቻ ነው የሚያዋጣው ማለታቸውና። በነ ስዩም መስፍንና ቴወድሮስ
አድሃኖም የሚመራው ሦስተኛው ብዱን ደግሞ። አስገብተን የማንሞክራቸው የሚል ወላዋይ የሆነ አቋም የያዙ እንደሆነና በዚህ መሰረት
ደግሞ ስብሰባው ያለመግባባት እንደተበተነ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል፣