Sunday, April 26, 2015

ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት “ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሊቢያ የሄዱ ኢትዮጵያዊያን ለሌላው መማሪያ ሆነዋል” በማለት በሚድያ የሰጠውን መግለጫ በመቃወም የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ።



ይህ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ገዥውን መንግስት በመቃወም የተካሄደ የሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ አንደኛው ከቂርቆስ ተነስቶ መስቀል አደባባይ የገባ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በርካታ ወጣት የተሳተፈበት ከልደታ ተነቶ ወደ ቤተመንግስት የገሰገሰ መሆኑን አስረድተዋል።
    በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እየተነሱ ከነበሩ መፈክሮች መካከል “ኢህ.አ.ዴ.ግ ሌባ፥ ለዜጎቹ የማይጨነቅ ስርዓት፥ ወጣቱ ትውልድ በሃገሩ ስራ ይፈጠርለት” የሚሉና ሌሎችም ሲሆኑ በዚህ  የተደናገጡት የስርዓቱ ባለስልጣናት የታጣቁ  ሃይሎችን በማሰማራት ሰልፈኛውን  መደብደብ ሲጀምሩ ህዝቡ በበኩሉም በዱላና በድንጋይ እየተከላከለ የገዥውን መንግስት ተላላኪ ታጣቂዎች በመጣስ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ለማወቅ ተችሏል።
     ይህ ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ከፍተኛ ማዕበል እንዳይሸጋገር የሰጉት ጠቅላይ ሚኒስተሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በየተራ ህዝቡን ለማረጋጋት ሲሉ ይህ በሬዲዮ የተላለፈ መግለጫ መንግስታችንን አይወክልም እኛ ጥልቅ በሆነ ሃዘን ላይነው ያለነው በማለት የኣዞ እንባ ማንባታቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ላልተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ከታህሳስ 14/ቀን/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት እውቅና እንደማይሰጠውና ለሚያካሂዱም በላያቸው ላይ ከባድ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ስርዓቱ በህገመንግስቱ ያሰፈረውን ራሱ እየተቃወመው እንደሆነ መረጃው በመጨረሻ አስረድቷል።