Wednesday, June 3, 2015

የመረብ ለኸ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ሰርቆ በልቷል ተብሎ በህዝብ ተከሶ እያለ ሊያዝ ባለመቻሉ ምክንያት ነዋሪው ህዝብ ተቃውሞ እንዳስነሳ ታወቀ።



ከወረዳው ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው የገዥው ህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  ቡድን ካድሬ የሆነው የመረብ ለኸ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክለአብ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ በመስረቁ  ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ/ም በነዋሪው ህዝብ ተከስሶ ምርጫው እስኪያልፍ በሚል ታስሮ የቆየ ሲሆን ምርጫው ካለፈ በኋላ ግን በነፃ ከመለቀቁ ባሻገር ወደ ክልል ተልኮ ከአባይ ወልዱ ጋር የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ሆኖ እንደተመደበ ለማወቅ ተችሏል።
   ነዋሪው ህዝብም ይህ ስልጣኑን ተጠቅሞ የህዝብንና የሃገርን ገንዘብ ያጠፋፋ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ መቀጣት አለበት አልን እንጂ ስልጣን አነሰው ጨምሩለት አላልንም በማለት ሃላፊነታችሁ እንደዚህ ከሆነ አስተዳዳሪ ስለማያስፈልገን ንግግራችሁን አንሰማም በማለት ተቃውሞ ማስነሳታቸውን ታውቋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደዚህ ዓይነት በሚሊዮን የሚቆጠር የህዝብና የሃገር ንብረት ከላይ እስከ ታች በሚገኙ ባለስልጣኖች ባላቸው ትስስር እየተጠፋፋ ድሃ ህዝባችን የዕለት ጉርስ አጥቶ በስደት የመንከራተቱ ጉዳይ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።