Wednesday, June 3, 2015

በማይፀብሪ ከተማ በሚገኘው ባንክ በጥበቃ ስራ ሲያገለግል የቆየ ሰራተኛ ያለምንም ምክንያት በመባረሩ ምክንያት ባባረሩት የገዥው መንግስት ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ ታወቀ።



    በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማይፀብሪ ከተማ በሚገኘው ባንክ የጥበቃ ሰራተኛ በመሆን ለረጅም ጊዜያት ሲያገለግል የቆየ ዜጋ ያለምንም ምክንያት “ከስራህ ተባርረሃል”  ስለተባለ የባንክ ቤቱን ስራ-አስኪያጅ ጨምሮ 6 የህወሃት አባላት የሆኑ ሰራተኞችን ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓም በጥይት የገደላቸው ሲሆን 3ቱን አቁስሎ ያልምንም ችግር ሊያመልጥ መቻሉን ተገለፀ።
   የጥበቃ ስራ እየስራ ቤተሰቡን ለአመታት ይመራ የነበረው ግለሰብ  የሰራበት የማስናበቻ የጡረታ ክፍያ ሳይታሰብለት  በአጋጣሚ ከስራው መባረሩ ሃላፊነታዊ ያልሆነ  እርምጃ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልፅ ቆይቶ ምንም ሰሚ ሊያገኝ ባለመቻሉ ምክንያት ይህን የመግደል ተግባር የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ እንደወሰደው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።