Wednesday, June 3, 2015

ዜና ጸረ ህዝብ የህወሃት ኢህአዴግን ተግባራት በመቃወም ወደ ትህዴን እተቀላቀሉ ያሉት ወጣቶች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መሆኑን ሪፖርተራችን ከትህዴን ማሰልጠኛ ገለፀ።



     በሪፖርተራችን መረጃ መሰረት ባለፈው ሳምንት ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ለትግል በመወሰን ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል  ከተቀላቀሉት  በርካታ ወጣቶች ማካከል-
  1.  ግርማይ መሰለ አስገዶም ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ጠራውር ቀበሌ፤ ሙኹዓት ሳዳ አካባቢ፤
  2.  አማንኤል ምሩቕ ወልዱና ሓዱሽ ደሳለኝ ገ/ሃንስ ሁለቱም ከምስራቃዊ ዞን፤ ጉሎመኻዳ ወረዳ፤ ዛላምበሳ ቀበሌ፤ አዲስ አለም አካባቢ፤
  3.  መሓሪ ተስፋማርያም ጉብሳ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ ገደና ቀበሌ፤ ዓዲ ጭዕንዶግ አካባቢ፤
  4. አመሩ ምስግና አብርሃ ከምስራቃዊ ዞን፤ ኢሮብ ወረዳ፤ ወርዓትለ ቀበሌ፤ ዳሮ አካባቢ፤
  5. ዜናዊ ገብረ ገብሩ፤ ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለከ ወረዳ፤ ጠራውር ቀበሌ፤ ምዳቕ ምፃይ አካባቢ፤
  6. ቴድሮስ ኪሮስ አበበ ከማእከላዊ ዞን፤ ታሕታይ ማይጨው ወረዳ፤ ዓዲገባት ቀበሌ፤ ድምዓሳኻ አካባቢ / በኤርትራ ውስጥ ከረን ከተማ ውስጥ ይኖር የነበረ/፤
  7.  ክብሮም ገብረሃንስ አርአያ ከማእከላዊ ዞን፤ አህፈሮም ወረዳ ዝባን ጒላ ቀበሌ፤ ጨጓሮ አካባቢ፤
  8. አብርሃለይ በየነ መንክር ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ መደባይ ጠረር ቀበሌ፤ ዓዲ ንአምን አካባቢ፤
  9. ገ/ዋህድ ገ/ገርግስ ታረቀ ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለከ ወረዳ፤ ጠረውር ቀበሌ፤ ሙኹዓት ሳዳ አካባቢ፤
  10. ሸዊት ግርማይ ሃይለ ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲፍታው ቀበሌ፤ ሓድሽዓዲ አካባቢ፤
  11. ዳዊት ፍትዊ ገ/ሃንስ ክማእከላዊ ዞን፤ አሕፈሮም ወረዳ፤ ጣብያ ገርሁ ስርናይ፤
  12. ዮውሃንስ አብርሃ ገ/ሚካኤል ከመቀሌ ዞን፤ ዓይደር ወረዳ፤ 03 ቀበሌ፤ ቀጠና 6 አካባቢ፤
  13. ብርሃኑ አፅበሃ ገ/አነንያ ከመቀሌ ዞን፤ ሃወልቲ ክፍለ ከተማ፤ ዓዲ ሽንድሑ ቀበሌ፤ ቀጠና 7 / በጅማ ዩንቨርስቲ የ 3 ዓመት ተማሪ የነበረ፤
  14. ጉዕሽ ወላይ ትንስኡ ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ፤ ሃድሽ ዓዲ አካባቢ፤
  15. ሰሎሙን ገ/መድህን ገ/ማርያም ከማእከላዊ ዞን፤ አሕፈሮም ወረዳ፤ ዕዳጋ ረቡዕ ቀበሌ፤ ዓዲ ቅሌቶ አካባቢ የሚገኙባቸው ሲሆኑ-
በአገራችን ውስጥ ስራ አጥነት ከመጠን በላይ እንደተስፋፋና ትምህርቱን የጨረሰ ተማሪ የስርዓቱ አባል ካልሆነ ስራ እንደማያገኝና በአሁኑ ጊዜ የወጣቱ ዋነኛ ምርጫ ስደት  መሆኑን በጅማ ዩንቨርስቲ የ3 ዓመት ተማሪ የነበረው ብርሃኑ አፅበሃ አስረድቷል።
   ተማሪ ብርሃኑ አፅበሃ በማስከተልም የጅማ ዩንቨርሲቲ እንደማንኛውም ያገራችን ትምህርት ቤቶች በብሄር፤ በዘር፤ በዘመድ አዝማድና በከባቢያዊነት  ትርምስ ላይ የሚገኝ ተቛም እንደሆነ በመግለፅ፤ በአባልነት ስም የሚሰጥ ነጥብም እንደ አንድ መደበኛ ትምህርት ተይዞ በኮርስ ደረጃ    እየተሰጠ እንደሆነ ገልጿል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩንቨርሲቲን የሚያህል ተቋም መደበኛና የተሟላ ቤተ መፅሃፍትና ቤተ ሙከራ እንደሌለው የነጥቡ አሰጣጥም ከሴቶቹ ጋር በሚፈፅሙት ፆታዊ ግንኝነት እንደሚያያዙትና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነች ሴት ግን ነጥብ ማግኘት እንደማትችል አክሎ አስረድቷል።
   አብርሃለይ በየነና ክብሮም ገብረዮሃንስ በበኩላቸው በምእራብ ትግራይ የእርሻ ቦታ እንዳይሰጥ መከልከሉንና የነዋሪነት ካርድና መንቀሳቀሻ ወረቀትም የምርጫው ቀን ሳያልፍ አትሰጡም በማለት ተከልክለው እንደነበር ገልጸዋል።
   ወጣቶቹ ባጠቃላይ በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በህዝቡ ላይ የተለያዩ ኢ-ሰብአዊ ግፎችን እየፈፀመ በመሆኑ ይህንን ስርዓት ለማስወገድ የትጥቅ ትግል እያካሄደ ከሚገኘው ትህዴን ጎን ሆነው ለመታገል እንደወሰኑ ከማሰልጠኛው ማእከል የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።