Wednesday, June 10, 2015

በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ከፍተኛ የዘይትና የስኳር አቅርቦት ችግር መኖሩን ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ አቤቱታ እያቀረበ ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።



   በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የስኳርና የዘይት አቅርቦት ከፍተኛ የሆነ ችግር ያጋጠመ ሲሆን ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም ምንም ዓይነት ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን የገለፀው መረጃው በተለይ በክልሉ የፍኖተ ሰላምና የባህርዳር ልዩ ዞን  ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም  አንዳንድ የዙሪያ ወረዳ ከተሞች ለችግሩ ተጠቂ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልፀው ከየከተሞቹ ከንቲባዎችና  የሚመለከታቸው አካላት ግን  የማይጨበጥ ተስፋ ከመስጠት በስተቀር ምንም አስቸኳይ መፍትሄ ሊያደርጉ አለመቻላቸውን ገልጿል።
   መረጃው ጨምሮም  በሁሉም ዞኖች እንደአማራጭ በሚል   በተመሳሳይ የቀረቡ ውስን የዘይትና የስኳር አቅርቦቶች የሚከፋፈሉት ለብአዴን ኢህአዴግ ቅርበት ባላቸው ካቢኔዎች ሱቅ ለድርጂት አባላቶች እንዲከፋፈል በመደረጉ በተቃዋሚነት አይን የሚታዩ በርካታ ዜጎችና ድሃ ወገኖች የችግሩ ተጎጂ መሆናቸውን አብራቷል።