Wednesday, June 10, 2015

በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ በተከሰተ የመብራት መቋረጥ ምክንያት በመብራት የሚሰሩ የግል ድርጂቶች ለኪሳራ መዳረጋቸውን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



    እንደ ምንጮቻችን ገለፃ መሰረት በጂግጂጋ ከተማ  የሚገኙ ከ12 ቀበሌ በላይ ህዝቦች ከዚህ በፊት መቆራረጡን ለመቀነስ እንደመፍትሄ በፈረቃ ይጠቀሙ የነበሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ከቀበሌ 1 እስከ ቀበሌ 5 ያሉት ነዋሪዎች  ለ6 ሰዓታት በአንድ ቡድን ከቀበሌ 5 እስከ ቀበሌ 9 የሚገኙት ደግሞ በተመሳሳይ በሌላ ፈረቃ እንዲሁም 3 ቀበሌዎች የመብራት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን አስረድተዋል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለም በፈረቃ ይጠቀሙ የነበረው መብራት ከነጭራሹ ከጠፋ 4 ቀናት ያስቆጠረ መሆኑንና በዚህ ሳቢያም በግል ወኪልነት የሚንቀሳቀሱ ድርጂቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን በምሬት ተናግረዋል።
   በሌላ በኩል በሶማሌ ክልል የሶማል ተወላጅ ወጣቶችና ሃበሻ በሚል የሚጠሯቸው በርካታ ነዋሪዎች ለምርጫ ከተመዘገቡ በኋላ ተወዳዳሪ በሌለበት አንመርጥም ብለው በግልፅ በመናገራቸው እየታሰሩ መሆናቸውን ያይን እማኞች ከስፍራው ገልፀዋል።